በስመ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

  • *በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ
  • *ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር በከተማ የምትኖሩ
  • *የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ
  • *በሕማም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችሁ
  • *እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በማረሚያ ቤት የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤

እንኳን ለ2004 ዓ.ም. የጌታችን፤ የአምላካችንና የመድሃታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ

ህዝቡ ቅርሶቹን መንከባከብና መጠበቅ እንደሚገባው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ አስገነዘቡ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንትና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንት በርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን በመሰራት ላይ ያለው ሙዚየምን ከጎበኙ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለጥንታዊ ቅርሶች ህልውናና ደህንነት መጨነቅና በዘመናዊ ሙዝየም ተሰባስበው የሚቀመጡበትን ሁኔታ መፍጠር ይገባዋል ብለዋል ፡፡

ጥንታዊያን ቅርሶቻችን የማንነታችን መገለጫ ብቻ ሳይሆኑ ለሀገራችን ገጽታ ግንባታ ትልቅ አስተዋጽኦ ያላቸው በመሆናቸው ቅርሶቻችንን በሚገባ ሁኔታ ማስቀመጥ፣ በተደራጀና ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ማስጐብኘት ይገባል ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ ዘመናዊ ሙዝየም በመገንባትና ለጐብኚዎች ምቹ ሁኔታን በመፍጠርም ገጽታችንን የበለጠ መገንባትና ከጐብኚዎች በሚገኘው ገቢም ድህነትን መዋጋት ይቻላል ብለዋል ፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያና ግብፅ በአሁኑ ወቅት ስላላቸው ግንኙነት አዲስ ሒደት በማጠናከር ዙሪያ ከግብፁ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አሳም ሸሪፍ ጋር ተወያዩ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዝዳንትና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንት፣ በግብፅ ባካሔዱት የ4 ቀናት ሐዋርያዊ ጉብኝት ከተለያዩ የአገሪቱ የመንግሥትና የሃይማኖት መሪዎች ጋር ተወያይተዋል ፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩ ከግብፁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አሳም ሸሪፍ ጋር ባካሔዱት ውይይት እንደተናገሩት ግብፅና ኢትዮጵያ ተፈጥሮአዊና ታሪካዊ እንዲሁም ሃይማኖታዊ ግንኙነት ያላቸውና ግንኙነቱም ለ16ዐዐ ዓመታት የዘለቀ መሆኑን አውስተው በዓለም እንደ ሁለቱ አገራት የረጅም ጊዜ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት አለመኖራቸውን ተናግረዋል ፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፤ በዓመት ሁለት ጊዜያት እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የመክፈቻው ሥርዓተ ጸሎት ከተፈጸመበት ከጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2004 ዓ.ም. ድረስ የተለመደውን ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባን በማካሔድ፤

ሀ. ለቤተ ክርስቲያናችንና ለኅብረተሰቡ የሚጠቅመውን፤

ለ. ለሀገርና ለዓለም ሰላም የሚበጀውን አጀንዳ በማመቻቸት በስፋትና በጥልቀት ተወያይቶ የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ዓመታዊ ምልዓተ ጉባዔ ተጀመረ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲወርድ ሲዋረድ በመጣው ሐዋርያዊ ትውፊት መሠረት የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ተከትሎ የሚካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ተጀመረ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ በቅዳሜ ዕለት ጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም ከ9፡00 ሰዓት ጀምሮ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በጸሎት የተጀመረ ሲሆን እሁድ ጥቅምት 12 ቀን 2004 ዓ፣ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል የተለመደውን ዓመታዊ የአባቶች ጸሎተ ፍትሀት ተካሂዷል፡፡

ሰኞ ጥቅምት 13 ቀን 2004 ዓ.ም መደበኛ የቅዱስ ምልዓተ ጉባዔ የመወያያ አጀንዳዎችን ቀርጾ በማጽደቅ ጉዔውን በተለመደው መንፈሳዊ ትውፊት መሠረት በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ

ሠላሳኛ መደበኛ ዓመታዊ ስብሰባ

ቃለ ጉባኤ

 

    አጠቃላይ ጉባኤው ከጥቅምት 7-11 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም. ተካሔዷል፡፡

  • • ጉባኤው በብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፣ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት፣ የዓለም ሃይማኖቶች ምክር ቤት ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ርእሰ መንበርነት፤
  • • በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የኢሉባቦርና የጋምቤላ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የስብሰባው መርሐ ግብር አስተባባሪነት የተካሔደ ሲሆን የጉባኤው አባላትም፣
  • • የመላ ኢትዮጵያ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት፣
  • • በውጭ ሀገር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳትና ተወካዮች፣
  • • ክቡራን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጆች፣
  • • የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪየውና ድርጅቶች ሓላፊዎች ፣
  • • የመላው አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፣
  • • የመላው አህጉረ ስብከት የካህናት፤ የምእመናን፤ የስብከተ ወንጌል፣ የሰበካ ጉባኤ አደራጆችና የሰንበት ትምህርት ቤቶች ተወካዮች ናቸው፡፡
  • • እንዲሁም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች የሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቃነ መናብርት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየሥራ ዘርፉ ሠራተኞች በተመልካችነት ጉባኤውን ተሳትፈዋል፡፡

    ተጨማሪ ያንብቡ

‹‹ገብረ ሰላመ በመስቀሉ››

‹ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ሰላምን አደረገ› ኤፌ. 2፡14-15

መለያየት የኃጢአት ውጤት እንደሆነ ሁሉ፣ አንድነት ደግሞ የሰለም፣ የፍቅርና የስምምነት ውጤት ነው ፡፡

የሰው ልጅ በተከተለው የተሳሳተ አማራጭ ከእግዚአብሔር ጋር የነበረውን ኅብረት ወይም ግንኙነት ሲያጣ ከሌሎች ፍጠረታት ጋር የነበረውን አንድነትም በተመሳሳይ አጥቶአል፤ ይልቁንም የእርስ በርስ መግባባት በመጥፋቱ የሰው ዘር በተለያየ ጎራ እየተሠለፈ በጥላቻ መተያየቱ የዘወትር ክስተት ሆነ ፡፡ተጨማሪ ያንብቡ

የዓለም አብያተ ክርስቲያናት የኤክስኪዩቲቭ ኮሚቴ ጉባዔ ለመጀመሪያ ግዜ በኢትዮጵያ ተካሄደ

ከመስከረም 1-5 ቀን 2004 ዓ.ም የተካሄደው ይህ ጉባዔ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ መክፈቻ ንግግር ተከፍቱዋል፡፡

ክቡራን የዓለም አብያተ ክርስቲያናት የኤክስኪዩቲቭ ኮሚቴ አባላት!

ወደ አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ እንኳን በደኅና መጣችሁ!

በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ቆይታችሁ ሥራችሁ፣ ጉባኤያችሁ የተቃና፣ ያማረ፣ የሰመረ እንዲሆን እንመኛለን፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ በሰሜን ምሥራቅ አፍሪካ በዓባይ ሸለቆ ዙሪያ በቀይ ባሕር አካባቢ የምትገኝ ጥንታዊት ታሪካዊት የክርስትና ሀገር ናት ፡፡ተጨማሪ ያንብቡ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !

  • • በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ፤
  • • ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትኖሩ፤
  • • የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
  • • በሕመም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
  • • እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት

ሰማይንና ምድርን፣ በውስጣቸው የሚገኙ ፍጥረታትን የሚታዩትንና የማይታዩትን የፈጠረ እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ከዘመነ ሉቃስ 2ዐዐ3 ወደ ዘመነ ዮሐንስ 2ዐዐ4 ዓ.ም. በሰላም አደረሳችሁ ፡፡

"ዘይሔድሳ ለምድር በበረከቱ"

"እግዚአብሔር አምላክ ምድርን በበረከቱ ያድሳታል /ድጓ/"

ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን እኛም እንደምንገነዘበው እግዚአብሔር አምላክ በፍጡራን አእምሮ ሊመጠን በማይችል በረከቱ ምድርንና በውስጧ ያሉትን ፍጥረታት ሁሉ በማያቋርጥ ሒደት እያደሰ ይኖራል ፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ፍጥረታት እየታደሱ እንዲተካኩ በማድረጉ የቀደመው ሲያልፍ አዲሱ ሲተካ የሕይወት ጉዞ የማያቋርጥ ሆኖ እንዲቀጥል አድርጎአል ፡፡ ከጌታችን ከአምላካችን ከመድኀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በፊት የነበረው አሮጌ ዘመን ዓመተ ፍዳ፣ ዓመተ ኩነኔ በእርሱ መሥዋእትነት ሲያሳልፍ ከልደተ ክርስቶስ ጀምሮ ያለውንም የምሕረት ዘመን ብሎ አድሶታል ፡፡ ወደፊትም በዳግም ምጽአቱ ሰማይንና ምድርን በማሳለፍ የተሻለ ሕይወት ለሰው ልጆች መስጠቱ የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ከቅዱስ ወንጌል ተምረናል ፡፡ (ማቴ. 24-25) በመሆኑም ፍጥረታትን የማሳለፉ ተግባር የእግዚአብሔር ቀዋሚ ሥራ ሆኖ እናገኘዋለን ፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን በባህርዩ ማርጀትና ኅልፈት የሌለበት ነው፤ በመጻኢው ዓለም ለሰው ልጆች ያዘጋጀው ሕይወትም ማርጀትና ኅልፈት የሌለበት፣ ሁል ጊዜ ሐዲስ ሆኖ የሚኖር ነው፡፡ የሃይማኖታችን ጽኑ ተስፋም በአዲሱ ዓለም ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ በደቡብ አፍሪካ የተገነቡትን የቤተ ክርስቲያኗን የትምህርት ተቋማትና የካህናት ማሰልጠኛ መርቀው ከፈቱ



ኢትዮጵያውያን በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገራት የሚያከናውኗቸውን የልማት ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳሰቡ ፡፡ በጆሀንስበርግ፣ በፕሪቶሪያ፣ በብሎምፎንቴን የተገነቡትን የትምህርት ተቋማትና የካህናት ማሰልጠኛ መርቀው የከፈቱት ቅዱስነታቸው እንደገለፁት ኢትዮጵያውያን ቀዳሚ ተግባራቸው በሥርዓትና በሕግ የተመሰረተ የጋራ ሥራና ተባብሮ ተረዳድቶ የመኖር ብሒል ያለው ዜጋ በመሆኑ ዛሬ ላይ የዓለም ምሳሌ በመሆን ቀዳሚ የሆነውን ልማት በመሥራት የወላጆቻቸው ልጆች መሆናቸውን አሳይተዋል ፡፡ ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል በማለት ገልፀዋል ፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ