የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከ3000 በላይ ለሚሆኑ ነዳያን የትንሣኤን በዓልን ምክንያት በማድረግ ለእያንዳንዳቸው የ100ብር እርዳታ አደረገች፡፡


በወቅቱ እርዳታው ሲሰጥ የነበረው ገጽታ

በስመ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

  • *በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ
  • *ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር በከተማ የምትኖሩ
  • *የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ
  • *በሕማም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችሁ
  • *እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በማረሚያ ቤት የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤

 

 

 

 

 

 

 

በትንሣኤው ትንሣኤያችንን ያበሰረን ጌታችን አምላካችንና መድሃኒችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለ2004 ዓ.ም. በዐለ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ፡፡

‹‹ ወይእዜኒ ክርስቶስ ቀደመ ተንሥኦ እምኩሎሙ ሰብ ሙታን››

‹‹አሁንም ክርስቶስ ከሞቱ ሰዎች ሁሉ አስቀድሞ ተነሥሮኣል›› (1ኛ ቆሮ 15፡20)ተጨማሪ ያንብቡ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ በአክሱም ጽዮን ማርያም እየተሠራ የሚገኘውን ሙዝየም የግንባታ ሂደት ጉብኝት አደረጉ፡፡ እንዲሁም ሆሳዕና በዓልን በደመቀ ሁኔታ አክብረው ተመለሱ፡፡

ለበለጠ ግንዛቤ የሚከተሉትን ቪዲዮዎችን ይመልከቱ፡፡


የአክሱም ጽዮን ሙዝየም ግንባታ ሂደት

ተጨማሪ ቪድዮ ይመልከቱ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

  • *በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ
  • *ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር በከተማ የምትኖሩ
  • *የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ
  • *በሕማም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችሁ
  • *እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በማረሚያ ቤት የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤

እንኳን ለጌታችን፣ ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የ2ዐዐ4 ዓ.ም. መዋዕለ ጾም በሰላም አደረሳችሁ፡፡

‹‹እብለክሙ በመንፈስ ሑሩ፤ ወፍትወተ ሥጋክሙ ኢትግበሩ››

‹በመንፈሰ ተመላለሱ እንጂ የሥጋችሁን ምኞት ከቶ አትፈጽሙ እላችኋለሁ›(ገላ 5፡16)ተጨማሪ ያንብቡ

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንና በኦሬንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት መካከል የተደረገው ዘጠነኛው ዓለም አቀፍ የጋራ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ፡፡

በኦሬንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናትና በሮም ካቶሊክ ቤተክርስቲያናት መካከል እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር ከ2003 ዓ/ም ጀምሮ የጋር የቲዎሎጂካል ውይይት ኮሚሽን ተመሠረቶ ያለማቋረጥ ለተከታታይ ስምንት ዓመታት ከሚመለከታቸው አብያተ ክርስቲያናት በተወከሉ አባላት መካከል ውይይት አድርጓል፡፡ ከአሁን በፊት የተደረጉት የስምንት ዓመታት ውይይቶች የተደረጉባቸው ቦታዎችም የመጀመሪያው ግብፅ ካይሮ፣ ሁለተኛው ሮም፣ ሦስተኛው አርማንያ ኤችሚያዚን፣ ዐራተኛው ሮም፣ አምስተኛው ሶርያ ማራት ኤዴንያ፣ ስድስተኛው ሮም፣ ሰባተኛው በአርመን ቂልቅያ ሥራ አንቴሊያስ ሊባኖስ፣ እና ስምንተኛው ጉባኤ ሮም ተከናውነዋል፡፡ ዘጠነኛውን ጉባኤ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ተከናውኗል፡፡

ዘጠነኛው ስብሰባ በአዲስ አበባ እንዲከናወን የሆነበት ሒደት...ተጨማሪ ያንብቡ

በስመ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

  • *በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ
  • *ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር በከተማ የምትኖሩ
  • *የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ
  • *በሕማም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችሁ
  • *እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በማረሚያ ቤት የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤

እንኳን ለ2004 ዓ.ም. የጌታችን፤ የአምላካችንና የመድሃታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ፡፡ተጨማሪ ያንብቡ

ህዝቡ ቅርሶቹን መንከባከብና መጠበቅ እንደሚገባው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ አስገነዘቡ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንትና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንት በርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን በመሰራት ላይ ያለው ሙዚየምን ከጎበኙ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለጥንታዊ ቅርሶች ህልውናና ደህንነት መጨነቅና በዘመናዊ ሙዝየም ተሰባስበው የሚቀመጡበትን ሁኔታ መፍጠር ይገባዋል ብለዋል ፡፡

ጥንታዊያን ቅርሶቻችን የማንነታችን መገለጫ ብቻ ሳይሆኑ ለሀገራችን ገጽታ ግንባታ ትልቅ አስተዋጽኦ ያላቸው በመሆናቸው ቅርሶቻችንን በሚገባ ሁኔታ ማስቀመጥ፣ በተደራጀና ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ማስጐብኘት ይገባል ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ ዘመናዊ ሙዝየም በመገንባትና ለጐብኚዎች ምቹ ሁኔታን በመፍጠርም ገጽታችንን የበለጠ መገንባትና ከጐብኚዎች በሚገኘው ገቢም ድህነትን መዋጋት ይቻላል ብለዋል ፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያና ግብፅ በአሁኑ ወቅት ስላላቸው ግንኙነት አዲስ ሒደት በማጠናከር ዙሪያ ከግብፁ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አሳም ሸሪፍ ጋር ተወያዩ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዝዳንትና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንት፣ በግብፅ ባካሔዱት የ4 ቀናት ሐዋርያዊ ጉብኝት ከተለያዩ የአገሪቱ የመንግሥትና የሃይማኖት መሪዎች ጋር ተወያይተዋል ፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩ ከግብፁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አሳም ሸሪፍ ጋር ባካሔዱት ውይይት እንደተናገሩት ግብፅና ኢትዮጵያ ተፈጥሮአዊና ታሪካዊ እንዲሁም ሃይማኖታዊ ግንኙነት ያላቸውና ግንኙነቱም ለ16ዐዐ ዓመታት የዘለቀ መሆኑን አውስተው በዓለም እንደ ሁለቱ አገራት የረጅም ጊዜ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት አለመኖራቸውን ተናግረዋል ፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፤ በዓመት ሁለት ጊዜያት እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የመክፈቻው ሥርዓተ ጸሎት ከተፈጸመበት ከጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2004 ዓ.ም. ድረስ የተለመደውን ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባን በማካሔድ፤

ሀ. ለቤተ ክርስቲያናችንና ለኅብረተሰቡ የሚጠቅመውን፤

ለ. ለሀገርና ለዓለም ሰላም የሚበጀውን አጀንዳ በማመቻቸት በስፋትና በጥልቀት ተወያይቶ የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ

ወደ ገፅ 1 2 >>