ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ በደቡብ አፍሪካ የተገነቡትን የቤተ ክርስቲያኗን የትምህርት ተቋማትና የካህናት ማሰልጠኛ መርቀው ከፈቱ



ኢትዮጵያውያን በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገራት የሚያከናውኗቸውን የልማት ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳሰቡ ፡፡

በጆሀንስበርግ፣ በፕሪቶሪያ፣ በብሎምፎንቴን የተገነቡትን የትምህርት ተቋማትና የካህናት ማሰልጠኛ መርቀው የከፈቱት ቅዱስነታቸው እንደገለፁት ኢትዮጵያውያን ቀዳሚ ተግባራቸው በሥርዓትና በሕግ የተመሰረተ የጋራ ሥራና ተባብሮ ተረዳድቶ የመኖር ብሒል ያለው ዜጋ በመሆኑ ዛሬ ላይ የዓለም ምሳሌ በመሆን ቀዳሚ የሆነውን ልማት በመሥራት የወላጆቻቸው ልጆች መሆናቸውን አሳይተዋል ፡፡ ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል በማለት ገልፀዋል ፡፡

 

 

 

 

 

 

 

በቴክኖሎጂ ፈጣን እድገት ምክንያት ዓለም ሰፊ ባልሆነችበት በዚህ ወቅት በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው እየተከናወነ ያለውን የልማትና የእድገት መርሐ ግብር ለማስፈፀም በሰፊው መነሳት አለባቸው ብለዋል ፡፡

በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን 2ዐዐ ተማሪዎችን የሚያስተናግድ ት/ቤት፣ በፕሪቶሪያ ኪዳነ ምህረት ከ1ዐዐ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የሚረዳ የቤተ ክርስቲያኗ የትምህርት ተቋማት የተገነቡ ሲሆን በብሎምፎንቴን ለኢትዮጵያውያንና ለደቡብ አፍሪካ ተወላጆች የሚሆን የቅዱስ ያሬድ የካህናት ማሰልጠኛ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ፡፡ቤተክርስቲያኒቱ የትምህርት ተቋሙ

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እስከ አሁን በውጭ ሀገራት ያሏትን የምዕመናን መገልገያ ስፍራዎች በማስፋት ሰፊ ሥራዎችን እያከናወነች ሲሆን ከኢየሩሳሌም ቀጥሎ በደቡብ አፍሪካ በ2ዐ,1ዐዐ ካሬ ሜትር ላይ የተመሰረተውን የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴና የቅዱስ ያሬድን ገዳም በመሥራት ሰፊ ሥራ መሠራቱ ተገልጾ በውጭ ያሉ ምዕመናን ወደ ሀገራቸው በመመለስ የሀገራቸውን የልማት ሥራ እንዲያፋጥኑ ምክር ተሰጥቷቸዋል ፡፡

በውጭ እየኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው በመመለስ የልማቱን ሥራ በማፋጠን ላይ ያሉ በመሆናቸው ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ደስተኛና ውጤታማ እንደሆኑ የተገለፀ ሲሆን፣ ቅዱስ ፓትርያርኩ በደቡብ አፍሪካ በተለያዩ ቦታዎች በመዘዋወር በሰጡት አባታዊ መልዕክትም ከሀገርና ከወገን ጋር ሆኖ ለሀገር ጥቅምና ለትውልድ የሚተላለፍ ሥራን መሥራት ይበልጥ የሚያስመሰግንና የሚያኮራ እንደሆነ አስገንዝበዋል ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ አፍሪካ ከ1892 ዓ.ም. ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠች ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅትም ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚያከናውኑትን መልካም ግንኙነት በማጠናከር ላይ ትገኛለች ፡፡

በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የተመራው የልዑካን ቡድን በደቡብ አፍሪካ ከመስከረም 5-8 2004 ዓ.ም ድረስ ያደረገውን ሐዋርያዊ የሥራ ጉብኝት አጠናቆ አዲስ አበባ ገብቷል ፡፡

እዚህ በመጫን ፎቶግራፍ ይመልከቱ፡፡