የቅዱሳን ሕይወት
ክፍል አንድ
ቅድስና በምንልበት ጊዜ ቅድስናን በሁለት ከፍሎ ማየት ተገቢ ይሆናል፤ ይኸውም፡-
ሀ. የባሕርይ ቅድስና ፤
ለ. የጸጋ ቅድስና ማለት ሲሆን የባሕርይ ቅድስና በምንልበት ጊዜ ለእግዚአብሔር ብቻ የምንገልጸው ልዩ አገላለጽ ነው፡፡ የጸጋ ቅድስና በምንልበት ጊዜ ደግሞ ሰማያውያን መላዕክትና ምድራውያን ሰዎች ራሳቸውን ለቅድስና አዘጋጅተው ሲገኙ ቅድስናውን የሚያገኙት የቅድስና ባለቤት ከሆነው ከእግዚአብሔር የሚገኝ ልዩ ስጦታ ነው፡፡ በተለይ ምድራውያን ሰዎች ነሃሃማተ ጸንተው፤ በበጎ ሥራ ተቃኝተው በቅን ልቡና አግዚአብሔርን ሲያገለግሉ ቅዱሳን ይሆናሉ፤ ቅዱሳንም ይባላሉ፡፡ ‹‹እኔ አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ›› ተብሏልና፡፡ (ዘሌ 19፡2)




